በረቂቅ ስያሜዉ ''ሎሬት ፀጋየ ገብረመድህን የአርት እና ምርምር ማዕከለ '' የተሰኘዉ ቤተ ጥበብ ሶስት የቲያትር አዳራሽ ፣ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ፣ ቤተመፅሀፍትን፣ የመሰብሰብያ አዳራሾችን ፣የፀጋዬ ባህላዊ ሙዝየምን ጨምሮ ሬስቶራንቶች እና የመዝናኛ ቦታዎችን ያካተተ ሲሆን አጠቃላይ የግንባታዉ ዲዛይን ባለቅኔዉ የኖረላትን ኢትዮጵያ መልክ ይዞ እንደሚገነባ አርክቲክት ሚካኤል በቀረፁት ዲዛይን አካተዋል። እዉቁ ኢትዮጵያዊ ባለቅኔ ፣ ፃህፈ ተዉኔት እና አንጋፋ የጥበብ ሰዉ ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን በህይወት ዘመኑ ባኖራቸው የጥበብ ስራዎቹ ስለአብሮነት ፣ ስለፍቅር እና ሰብዓዊነት በማይነጥፈዉ ብዕሩ ሲያስተምር የኖረ እና በጥበብ ማማ ላይ ከፍ ብሎ ያለ የአርት ሰዉ መሆኑን የሚናገረዉ የሙያ ባልደረባዉ እና ሌለኛው አንጋፋ የጥበብ ሰዉ አርቲስት አበበ ባልቻ በስሙ የሚገነባው የአርት እና የምርምር ማዕከል አእላፍ ኢትዮጵያዊ ፀጋዬዎች የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን ነዉ የጠቆመው።በረቂቅ ዲዛይኑ ላይ የመከሩት አንጋፋው አርቲስት ተፈሪ አለሙን ጨምሮ በርካታ የጥበብ ሰዎች እና የአምቦ ዩንቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ታደሰ ቀነዓ ለማዕከሉ ግንባታ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች በአጭር ግዜ ተሰብስበው ወደስራ የሚገባበት አግባብ ላይ የድርሻቸውን እንደሚወጡ ጠቁመዉ መላዉ ኢትዮጵያዉያን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል።ቀደም ብሎ በተለያዩ ዝክረ ፀጋዬ ሁነቶች እና በጥበብ ስራዎች ላይ በስፋት ወደስራ የገባው በአምቦ ዩንቨርስቲ የፀጋዬ ገብረመድህን የአርት እና ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር ተባባሪ ፕሮፌሰር ሳሙኤል ለይኩን ማዕከሉ የሎሬቱን ሀገራዊ የአርት ስራዎችን ከመዘከር በጎላ መልኩ ኢትዮጵያዉያንን በጥበብ ፣ በባህልና በታሪክ አጋምዶ ወደ ቀድሞው የልዕልናዋ ማማ ጫፍ ለማድረስ ሀያሌ ስራዎችን በመሰራት ላይ መሆኑን ነዉ ያስታወቁት።የአርት እና ምርምር ማዕከሉ የመጀመርያ ንድፍ ዲዛይን ላይ የመከሩ ባለድርሻ አካላት ለግንባታው ተጨማሪ እሴት የሚሆኑ ሀሳቦችን በመሰንዘር ለዕቅዱ ስኬት እንደሚሰሩም ነዉ የተናገሩት።
የቪዲዮ ምስሉን ለመመልከት ከታች ያለዉን የቴሌግራም መስፈንጠሪያይጫኑ
https://t.me/soldare2ndm/302
https://youtu.be/hPp_4tOCXGQ