ከጭቃ ስልክ ከመስራት ፤ 3 አለም አቀፍ የፈጠራ ፓተንቶች እና ከ30 በላይ አዋርዶችን ከመሸለም አልፎ የህቡዕ ቴክኖሎጂ ማዕከል የሆነዉ የናሳ የምርምር ማዕከል አባልነት የደረሰው ወጣት እስራኤል ቤለማ።ወጣቱ ተወልዶ ያደገው በኦሮሚያ ክልል ደንዲ ወረዳ ጊንጪ ከተማ ሲሆን የፈጠራ ስራዉን ገና በለጋ እድሜው ነዉ የጀመረው ።ልጅ ሳለ ሰዎች በስልክ ሲነጋገሩ ያያል። 'እንዴት ድምጽ በቀጭን ሽቦ ይተላለፋል?' ሲል በጠያቂ አእምሮው ያሰላስላል። አውጥቶ አውርዶም ስልክ ለመፈልሰፍ ይወስናል።ያስፈልጉኛል ያላቸውን እቃዎች ከአካባቢው መሰብሰብ ጀመረ። ጣሳን ለድምጽ መሳቢያነት ተጠቅሞ ከጭቃ የተሰራ የስልክ እጀታ ሠራ።ስልክ የመጀመሪያ የፈጠራ ሙከራው አይደለም። ዘወትር አዳዲስ ነገር ስለመፈልሰፍ ከማሰብ ወደ ኋላ አይልም። እስራኤል ቤለማ ይህ ባህሪው የኢንጂነርነት ሙያን ለመቀላለል እንዳበቃው ይናገራል። ኢትዮ ቴለኮምን ጨምሮ የሃገር መከላከያ ሰራዊት ሚንስቴርን በፈጠራ ስራዎቹ ያገለገለዉ ወጣት እስራኤል ቤለማ ዛሬ ላይ የናሳ ተቋም ዉስጥ የምርምር ስራ ላይ ተሰማርቶ ይገኛል።